የሀዘን መግልጫ

ዶ/ር አሸብር ሱራፌል በድሬዳዋ ተወልደው ያደጉ ሲሆን የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ በባህርዳር ፖሊቴክኒክ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በኢንዱስትሪ ኬሚስትሪ ዲፕሎማ ተቀበሉ፡፡

በድሬደዋ ኖትር ግድብ ትምህርት ቤት እና በአዲስ አበባ ናዝሬት ሁለተኛ ደረጃ ት / ቤት በኬሚስትሪ መምህርነት ለ 4 ዓመታት ከሠሩ በኋላ ወደ ሮማኒያ ሄደው ሂውማን ሜዲስንተማሩ፡፡ ከሮማኒያ ከተመለሱ በኋላ ጋምቤላን ፣ ወላይታ ሆስፒታልን እና አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ማዕዘናት በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች የጠቅላላ ሐኪም ሆንውም አገልግለዋል፡፡

ዶ/ር አሸብር ሱራፌል

በመቀጠል በፅንስና በማህፀን ሕክምና ትምህርታቸውን ለመከታተል ወደ ሩማንያ ተመልስው በተሳካ ሁኔታ ካጠናቀቁ በኃላ በአሰላ ሆስፒታል የፅንስና ማህፀንና ህክምና ባለሙያነት አገልግለዋል፡፡ከአስር ዓመታት በላይ በሆስፒታሉ ውስጥ ብቸኛ የማህፀንና ፅንስ ሃኪም ባለሙያ የነበሩ ሲሆን ብዙ እናቶች ከሞት ታድገዋል::

በተጨማሪም በርካታ ወጣት የጤና ባለሙያዎችን በማሰልጠን ብዙዎች የእርሳቸዉን ፈለግ እንዲከተሉ አነሳስተዋል፡፡የኢትዮጵያ ህክና ማህበር ከሶስት አስርት ዓመታት በላይ የሴቶችን የስነ ተዋልዶ ጤና ለማሻሻል ስራቸውን እና ህይወታቸውን በሰጡት በዶ/ር አሸብር ሱራፌል ህልፊት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰቦቻቸው ለወዳጅዘመዶቻቸው እንዲሁም ልስራ ባልደረቦቻቸው መፅናናትን ይመኛል::