የነሐሴው ነጻ የሕክምና አገልግሎት

በክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር ከጌራ የቤት ለቤት ሕክምና እና የሐኪሞች ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ግቢ ውስጥ ለሕክምና መክፈል ለማይችሉ የማህበረሰብ ክፍሎች የነፃ ህክምና አገልግሎት ሰጠ፡፡


ማህበራችን መርሃግብሩ የውስጥ ደዌ፣ የቀዶ ጥገና፣ የቆዳ፣ የዓይን፣ የጥርስ፣ የአእምሮ ሕክምና እና የማኅጸንና ጽንስ ሕክምና ስፔሻሊስቶችና ጠቅላላ ሐኪሞች አንዲሁም በሌሎች የጤና ባለሙያዎች ጋር በጋራ በመሆን አገልግሎቱ እንዲሰጥ አስተባብሯል፡፡ የተሟላ የላብራቶሪ፣ የራጅና የአልትራሳውንድ አገልግሎት በቦታው ላይ እንዲሰጥ በአለርት ኮምኘሬንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልና በአካባቢው የሚገኙ ፋርማሲዎች፣ ክሊኒኮችና ጤና ጣቢያዎች ሪፈር የሚደረጉ ታካሚዎችን በመቀበል ከፍተኛ ትብብር አድርገዋል።በእለቱ ሕክምናውን ያገኙ የማህበረሰብ ክፍሎች ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሃሳባቸውን ሰጥተዋል፡፡የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ ይህንን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሰጡ የሕክምና ባለሙያዎች የምስክር ወረቀት ከምስጋና ጋር አበርክቶላቸዋል፡፡