የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር 59ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤው

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር 59ኛውን ዓመታዊ የሕክምና ጉባኤውን “በዘመናዊ የሕክምና አገልግሎት አሰጣጥ የሙያ ማህበራት ፣ የሐኪሞች፣ የማህበረሰቡና የባለድርሻ አካላት ኃላፊነትና ግዴታዎች እንደዚሁም እድሎችና ተግዳሮቶች” በሚል መሪ ቃል አካሂዷል፡፡
በመርሃግብሩ በክብር እንግድነት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣ የማህበሩ አባላት፣ ስፔሻሊቲ ሶሳይቲ እና የአጋር ድርጅቶች ተወካዮች ታድመውበታል፡፡


በጉባኤው ላይ የጠቅላላ ጉባዔው አባላት በቀጣይ ሶስት ዓመታት ማህበሩን የሚመሩ የቦርድ አባላትን ምርጫ አካሂዷል፡፡
በዚህ መሰረት ዶ/ር ተግባር ይግዛው የማህበሩ ፕሬዝደንት፣ ዶ/ር አማል ሳለህ ምክትል ፕሬዝደንት እና ዶ/ር አንዱአለም ደነቀ ዋና ጸሃፊ ሆነው ሲመረጡ ፕሮፌሰር አመዘነ ታደሰ፣ ዶ/ር ባህሩ በዛብህ፣ዶ/ር ናታን ሙሉብርሃን እና ዶ/ር አቤኔዘር ትርሲት የቦርድ አባላት ሆነው ተመርጠዋል፡፡
በዚህ አጋጣሚ ማህበሩ ለተመረጡት የቦርድ አባላት እንኳን ደስአላችሁ እያለ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላችሁ ምኞቱን ለመግለጽ ይወዳል፡፡

Learn, Network and Grow!
Powered by EMA