የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ጳውሎስ ቁአና አረፉ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም የሆኑት እና የኢተዮጵያ ሕክምና ማህበርን በፕሬዝዳንትነት የመሩት ዶክተር ጳውሎስ ቁአና በ97 ዓመታቸው አረፉ፡፡

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል መስራች የሆኑት እንዲሁም የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርን በፕሬዝዳንትነት እ.አ.አ ከ1971 እስከ 1976 የመሩት ታዋቂው ባለሙያ ዶክተር ጳውሎስ ቁኣና በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ከሊባኖሱ ቤሩት አሜሪካዊ ዩኒቨርሲቲ በዓይን ሕክምና የተመረቁት የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፣ በ1956 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 1964) በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል።
የትምህርት ክፍል መስራች፡ በኢትዮጵያ ያለውን ከፍተኛ የዓይን ሐኪሞች እጥረት ለመቅረፍ በ1972 ዓ.ም (እ.ኤ.አ 1980) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ስፔሻሊቲ (ሬዚደንሲ) ፕሮግራምን አስጀምረዋል።

የሀገር ፍቅር አርአያነት፡ በውጭ ሀገራት በርካታ የሥራና የሀብት አማራጮች ቢቀርቡላቸውም፣ “በቂ የሕክምና ዶክተሮች የሉንም” በማለት ሀገራቸውን ጥለው ሳይወጡ ሙሉ ዕድሜያቸውን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ገብተዋል።

የማኅበር መስራች፡ የኢትዮጵያ የዓይን ሕክምና ማኅበር እንዲመሠረትና በዘርፉ የምርምር ልውውጥ እንዲዳብር ግንባር ቀደም ሚና ተጫውተዋል።

በዶክተር ጳውሎስ ጥረትና መሠረት ጣይነት የተጀመረው የትምህርት ክፍል እስከዛሬ ድረስ 118 የዓይን ሐኪሞችን አፍርቶ ለሀገር ማበርከት ችሏል።

የዚህ ታላቅ የሀገር ባለውለታ የቀብር ሥነ-ሥርዓት ክብራቸውን በጠበቀ መልኩ የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቶለት እንደሚፈጸም ታውቋል።

የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር በዶክተር ጳውሎስ ቁአና ህልፈተ ህይወት የተሰማዉን ሃዘን እየገለጠ ለቤተሰቦቻቸዉ፣ ወዳጆቻቸዉና ለመላው የሕክምና ማኅበረሰብ ፈጣሪ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።
ጳውሎስ ቁአና በ97 ዓመታቸው አረፉ
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የዓይን ሐኪም እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የዓይን ሕክምና ትምህርት ክፍል መስራች የሆኑት እንዲሁም የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርን በፕሬዝዳንትነት እ.አ.አ ከ1971 እስከ 1976 የመሩት ታዋቂው ባለሙያ ዶክተር ጳውሎስ ቀንኣ በ97 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።