የኮቪድ 19 ክትባትን

የኢትዮጵያ ሕክምና ማሕበር ከጤና ሚኒስቴር እና ሪዞልቭ ቱሴቭ ላይቭስ ጋር በመሆን የጤና ልማት ሰራተኞች የኮቪድ 19 ክትባት በመውሰድ ተጋላጭነታቸውን እንዲቀንሱ ለማድረግ የጀመረውን ስራ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል፡፡

የኮቪድ 19 ክትባትን አስመልክቶ ያለውን የአመለካከት ክፍተት መቅረፍ ስለሚቻልበት ሁኔታ ላይ የሚመክር መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ለባለድርሻ አካላት እና ለሚመለከታቸው የስራ ኃላዎች ገለጻ ተሰጥቷል፡፡

በገለጻ መርሃግብሩ ላይ በጤና ተቋም ውስጥ የሚሰሩ የጤና ልማት ሰራተኞች የማህበረሰባችንን ጤና ለማስጠበቅ በሚያደርጉት ጥረት ውስጥ መረሳት የሌለበት ተጋላጭነታቸውን ግምት ውስጥ በማስገባት የኮቪድ 19 ክትባትን መውሰድ እንዳለባቸው የተገለጸ ሲሆን ለሌሎችን የምንመክረውን አድርገን አብነት ሆነን ማሳየት በዚህ ዙሪያ እንደ ሃገር ለማምጣት የምንፈልገውን የአመካከት ለውጥ ለማምጣት ቀላል ያደርገዋል ተብሏል፡፡

ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ የኮቪድ 19 ክትባትን አስመልክቶ ያሉ አመለካከቶችን እና ሊወሰድ ስለሚገባው የመፍትሔ እርምጃዎች በጥናት የተደገፈ ገለጻም ተደርጓል፡፡