የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት

የዓለም የጡት ማጥባት ሳምንት ከሐምሌ 25 – ነሐሴ01 ይከበራል፡፡ የእናት ጡት ወተት መተኪያ የሌለው ተፈጥሯዊና የመጀመሪያ ተስማሚ የህጻናት ምግብ ነው፡፡ ለጨቅላ ሕፃናት ጤና ተስማሚ የሆኑ ሁሉንም ንጥረነገሮች አካቶ የያዘ ነው፡፡ በእናትና ልጅ መካከል ሊኖር የሚገባውን ጤናማ ትስስርም የሚያጠናክር ነው፡፡

የእናት ጡት ወተት እጅግ ጠቃሚ የሆነ የምግብ ዓይነት ሲሆን ጨቅላ ሕፃናት ከተወለዱ ከ1 ሰዓት በኋላ ጀምረው ለተከታታይ 6 ወራት የጡት ወተት ብቻ መጥባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተለያዩ የህፃናት በሽታ በመከላከል የሀገሪቱን የጤና ወጪ ይቀንሳል በተፈጥሮ ስለሚገኝ ወጪ ቆጣቢ ነው፡፡