ዶ/ር አህመድ መሐመድ

በህይወት ዘመን የላቀ የሙያ አገልግሎት

በሐረሪ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ሐረር ከተማ ነው የተወለዱት፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርታቸውን በሐረር ከተማ ቤተልሄም ትምህርት ቤት እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በወንጂ ቁጥር 2፣ በአዳማ አፄ ገልውዲዎስ እና በሐረር ተከታትለዋል፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ እና የሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊቲ ትምህታቸውን ተከታትለዋል፡፡

ለ35 አመታት በዋርዴር ጤና ጣቢያ፣ በቀብሪ ደሀር ሆስፒታል፣ በጎዴ ሆስፒታል በባለሙያነትና በሃላፊነት እንዲሁም በሶማሌ ክልል ጤና ቢሮ የበሽታ ቁጥጥር እና የመከላከል ክፍል እንዲሁም በካራማራ ሆስፒታል በሕፃናት ሕክምና ስፔሻሊስትነት ሰርተዋል፡፡ አሁን በጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ ሼኽ ሀሰን የቤሬ ቲቺንግ ሆስፒታል በመምህርነት እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡

ዶ/ር አህመድ መሐመድ፤ በህይወት ዘመን ላበረከቱት የላቀ አገልግሎት ጤና ሚኒስቴር በ27ኛው የጤና ዘርፍ አመታዊ ጉባኤው ተሸላሚ አድርጎ መርጧቸዋል