ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት እየተከሰቱ ባሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የግንዛቤ ስራ መሰራት እንዳለበት ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ዙሪያ የሚያደረገዉን ማህበረሰቡን የማንቃት እና የማስተማር እንቅስቃሴን በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ ለማስቀጠል በጤናዉ ዘርፍ እየሰሩ ካሉ 12 ሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች እና ሙያ ማህበራት ጋር ጥምረት ለመፍጠር የመጀመሪያዉን ስብሰባ በሳሮ ማሪያ ሆቴል ማካሄዱ ይታወሳል።

በመሆኑም የጥምረቱ አባል ማህበራት በጤናማ ያልሆኑ ምግቦች ና እያስከተሉ ባለዉ የጤና ኢኮኖሚያዊና ማህበረሰብያዊ ጫና፣ ዙሪያ በቂ መረዳት እንዲኖር በግንቦት 12እና 13 በአዳማ ስልጠና ተሰጥቷል። ከዚህም ባሻገር ወደፊት ጥምረቱ ስለሚሰራቸው ስራዎች እና ከእያንዳንዱ የጥምረቱ አባል ምን እንደሚጠበቅ በጥልቀት ተወያይተዋል።ወ/ሮ ትእግስት መኮንን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር በበኩላቸው የጥምረቱ አባላት በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት ስልጠናው ላይ በመገኘታቸው አመስግነው በጋራ ሆነን ለውጥ ለማምጣት ተከታታይነት ያለው ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል፡፡