EMA news

 
 
ሚያዚያ 3/2011 ኢ.ሕ.ማ. የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ከዚህ በፊት ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ በርካታ ሰልጣኞችን በህክምና ተቋማት መድቦ አለማሰራት አሳሳቢ እንደሆነበት መግለጹ ይታወሳል፡፡
 
ከዚህም ጋር ተያይዞ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ችግሩ እልባት እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን በዛሬው እለት የጤና ሚኒስቴር ተመርቀው ስራ ያልያዙ ከ 450 በላይ ሃኪሞችን ምደባ ማካሄድ መጀመሩን የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርም ለማወቅ ችሏል፡፡
 
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርም ለዚህ ውጤት መድረስ ሚና ለነበራቸው ፤ሀኪሞችን በመወከል ጥረት ሲያደርጉ ለነበሩት ና ለጤና ሚንስቴር አመራሮች ምስጋናውን ያቀርባል፡፡
 
ማህበሩ የህክምና የባለሙያዎቹን የምደባ ሂደትና ከምደባ በኋላ በአግባቡ ስራ እንዲጀምሩ መደረጋቸውን በመከታተል ያሉትን ሁኔታዎችን የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
 
የጤና ሚኒስቴርም ሀገሪቱ የሰለጠነ የህክምና ባለሙያ እንደሚያስፈልጋት ቢያምንም የባለሙያዎች ቅጥርን ለማከናወን የበጀት እጥረት እንዳለበት እንደ አንድ ምክንያት ሲጠቅስ ቆይቷል፡

መጋቢት 28/2011 ኢ.ህ.ማ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ በሀገሪቱ ጥራት ያለው የጤና አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ `ለህክምና ባለሙዎች የተሰጠው ትኩረት በቂ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡


ፕሬዝዳንቱ ይህንን ያሉት የደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ ያሰለጠናቸውን 42 ሐኪሞችን ባስመረቀበት ወቅት ነው፡፡


ፕሬዝዳንቱ በአሁን ሰዓት ከተለያዩ ትምህርት ተቋማት ተመርቀው የወጡ በርካታ ሰልጣች ቢኖሩም በመንግስት በኩል በህክምና ተቋማት መድቦ አለማሰራት አሳሳቢ እንደሆነም ነው የተናገሩት፡፡
በተለይም ጥራት ያለው ህክምናን ተደራሽ ለማድረግ ሀገሪቱ የሰለጠነ የህክምና ባለሙያ ብትፈልግም የባለሙያዎች ቅጥርን ለማከናወን ከበጀት እጥረት ጋር ተያይዞ የሚነሳው ጉዳይ ጥያቄ እንደሆነባቸው ነው የገለጹት፡፡
ለዚህ ደግሞ የሚመለከታቸው አካለት ትኩረት ሊያደርጉበት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡

“አገራችንና ህዝባችን ገና ብዙ ሀኪሞችንና የጤና ድርጅቶችን እንደሚፈልግ ይታወቃልና እባካችሁ አሁን በመቶዎችና ከጥቂት ወራት በኋላ ደግሞ በሺዎች የሚቆጠሩ ሀኪሞችን ስራ አጥ አታድረጓቸው፤ ጤና መሰረታዊ ፍላጎት ነው ከማለት አልፋችሁ በቂ በጀት በጅቱለት፤ በዚች ደሃ አገር ሀኪም ስራ አጥቶ ሰላማዊ ሰለፍ ወጣ ተብሎ መሳቂያ መሳለቂያ አንሁን እላቸዋለሁ፡፡”

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በተለይም የጤና ባለሙያዎች የሚጠበቅባቸውን አገልግሎት ለመስጠት እያጋጠማቸው ያለውን ችግሮችና ለጤናው ዘርፍ ፈተና የሆኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥያቄዎችን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፤ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ለክልል ፕሬዘዳንቶች ለማቅረብ መዘጋጀቱንም የማህበሩ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ገመቺስ ማሞ ተናግረዋል፡፡


ዶ/ር ገመቺስ ማሞ በምርቃቱ ወቅት ባደረጉት ንግግር ተማሪዎች በስልጠና ወቅት የሚጋጥማቸው የትምህርት መሳሪያዎች ግብኣት አለመሟላት ፤ የመምህራን እጥረት ዘርፉን ከመጀመሪው እየገጠመው ያለው ወሳኝ ፈታናዎች ናቸው ብለዋል፡፡

" የዛሬ ተመራቂዎች ፈተናዎችን አልፋችሁ ነው ለዛሬዋ ቀን የደረሳችሁት፡፡ ሌላው ቢቀር ባንድ ወቅት ተፈጥሮ የነበረው የአስተማሪ እጥረት እና በቅርቡ ተፈጥሮ የነበረው የኢንተርንሺፕ እሰጥ አገባ የሚረሱ አይደሉም፡፡”

 

Download the whole Speech

https://drive.google.com/open?id=1mCi4t36uni5H4QUG_XCz5aqABxHO6lAu

Ethiopian Medical Association would like to extend a huge thank you to our
partners for their special collaboration during the 55th Annual Medical
Conference & International Health & Wellness Exhibition.

Your investment and support is greatly appreciated.

Thanks again

 

     

Ethiopian Medical Association warmly invites its members to join EMA’s special business meeting.

The meeting is of the essence to help in shaping the future of healthcare service.

With an exciting line-up of experts who will challenge, engage and debate on the current face up to private health sector and Young graduates.

Date: On Feb 21, 2019
Place: @ Rift valley university college Geda campus, Gotera area 
Time: from 8:30AM -5:00PM

Attention: the place is limited to only 100 members on first comes first served principle.

Please don't apply if you are not sure of your attendance because no-show-up means wasting the resource for reservation and opportunity of others

To secure your spot at the meeting, register today by following the link below.

https://goo.gl/forms/TLN6kRHVEQypAGXn2

"Donate for wellness"  

This year Ethiopian Medical Association will host its 55th Annual Medical Conference and International Health and Wellness Exhibition from February 22 – 24, themed “Outreaching Universal Health Coverage : the Ethiopian perspective.”

As part of the program an important initiation for a life-saving cause is expecting to see a higher number of participation.

What: Special blood donation Event
The day is not just about collecting blood, but also raising awareness on why it is important to donate.

Who: This year we are having list of blood donors such as; Health Ministers, hospital CEO, senior physician, Executive Committee and Members of Ethiopian Medical Association etc.

When: February 22/2019

Time: During the opening ceremony of the 55th annual medical conference of EMA

Where: Ethiopian Youth sports Academy
Kindly contribute in the same. All interested volunteers will have the opportunity to donate blood!

Click on the details of the Events; https://emaconference2019.org

Vision

To see a healthy and prosperous Ethiopian community who access quality health services through enhancing physicians’ professional capacity and guarding the rights and benefits of medical professionals so that professionals would be enthusiastic to discharge quality services and respect professional ethics. 

Mission

EMA’s mission is to:

  • Ensure that the community gets quality heath service and care;
  • Promote the highest standards in medical education, science, art and practice and
  • Ensure the rights and benefits of medical professionals (doctors) and act as their voice.
     
       
     

kirkos Sub-City
Roosevelt street, Infront of africa union main gate
Tel: 251 115 521776/251 115 547982
Fax: 251 115 151005
email: ethiopianmed@gmail.com
www.ethiopianmedicalass.org
Copyright © Ethiopian Medical Association 2010 All rights Reserved.