ዶክተር ንጉስ ሸጋው ከባህር ዳር ከተማ 43ኪ.ሜ ርቆ በሚገኘው አዴት ሆስፒታል ለህብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጥ ባለሙያ ነበር፡፡ ባጋጠመው የደም ካንሰር ህመም ምክንያት በጥቁር አንበሳ ሪፍራል ሆሰፒታል ውስጥ ህክምናውን ሲከታተል ቆይቷል፡፡ በተደረገለት ምርመራም የህመሙ ደረጃ ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ መታከም እንዳለበት የሚያሳይ በመሆኑ በቤተሰቦቹ እና በሙያ አጋሮቹ ለመታከሚያ የተጠየቀውን ገንዘብ የማሰባሰብ ስራ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

 

በዚሁ አጋጣሚ ማህበራችን ሀኪሞች እና ሌሎች የጤና ባለሙያዎች ተመሳሳይ ሁኔታ በሚፈጠርበት ወቅት የጤና መድህን ዋስትናችው መጠበቅ እንዳለበትና የህክምና ወጪአቸው ሊሸፈንላቸው እንደሚገባ ያምናል፡፡ ሆኖም በዚህ ሰዓት ይህን አገልግሎት ሊየገኙ የሚችሉበት አሰራር እስካሁነ ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ ለሃኪሞች ብሎም ለጤና ባላሞያዎች የጤና መድን ሽፋን መተግበርን እና መሰል ጉዳዮችን በተመለከተ ሴክተር መስሪያ ቤቶች በዘላቂነት መፍትሄ እንዲያበጁ ለማሳሰብ እንወዳለን፡፡ ማህበሩም ይህንን በተመለከተ በቋሚነት መፍትሄ ለማምጣት የጀመርነውን እንቅስቃሴ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን አጠናክረን እንቀጥላለን፡፡ ለዶክተር ንጉስ ሸጋው ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመድ እና የሙያ አጋሮች መጽናናትን እንመኛለን፡፡

Vision

EMA envisions seeing a healthy and prosperous Ethiopian community with access to quality health services.

Mission

EMA’s mission is to:

  • Ensure that the community gets quality heath service and care;
  • Promote the highest standards in medical education, science, art and practice and
  • Ensure the rights and benefits of medical professionals (doctors) and act as their voice.

kirkos Sub-City
Roosevelt street, In-front of Africa Union main gate
Tel: 251 115 521776/251 115 547982
Fax: 251 115 151005
email: ethiopianmed@gmail.com
www.ethiopianmedicalass.org
Copyright © Ethiopian Medical Association 2020 All rights Reserved.