የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር በዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ ተስፋሚካኤል (ተባባሪ ፕሮፌሰር) ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልጻል፡፡ ዶክተር ፍሰሃየ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የህብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት በኢፒዲምዮሎጂ ትምህርት ክፍል ባልደረባ የነበሩት ሲሆን የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሞያቸው ሕብረተሰባቸውን በማገልገል ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ በሽታ ታመው የሕክምና እርዳታ ሲደረግላቸው ከቆዩ በሃላ በቀን 01/12/2012 ዓ/ም ከዚህ ዓለም በድንገት በሞት ተለይተዋል፡፡
 
 
ዶ/ር ፍሰሃየ በእናቶችና ህፃናት ህክምና፣ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች፣ በስነ-ምግብ፣ በወባ፣ በኤች አይቪ ኤድስና ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ጨምሮ በሌሎች የሕብረተሰብ ጤና ዘርፎች ከ50 በላይ ችግር ፈቺ ጥናቶችን በታዋቂ ጆርናሎች በማሳተም አዳዲስ እውቀቶች በማፍለቅ ለዓለም አሻራቸውን አሳርፈዋል።
 
ዶክተር ፍሰሃየ አለምሰገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሺኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር በአክሱም ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ ፈጣን ግብረ መልስ ቡድን መሪ በመሆን ህዝባቸውን ከቫይረሱ ለመታደግ ሌተቀን ሲሰሩ ቆይተው የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ባደረገላቸው ጥሪ በኮሮና ቫይረስ መረጃ ትንተና እና ትንበያ ክፍል በመስራት ላይ እያሉ በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ህክምና ሲደረግላቸው ቆይቶ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
 
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ለቤተሰቦቻቸው፣ ለስራ ባልደረቦቻቸውና ለጓደኞቻቸዉ መፅናናትን ይመኛል።

Vision

EMA envisions seeing a healthy and prosperous Ethiopian community with access to quality health services.

Mission

EMA’s mission is to:

  • Ensure that the community gets quality heath service and care;
  • Promote the highest standards in medical education, science, art and practice and
  • Ensure the rights and benefits of medical professionals (doctors) and act as their voice.

kirkos Sub-City
Roosevelt street, In-front of Africa Union main gate
Tel: 251 115 521776/251 115 547982
Fax: 251 115 151005
email: ethiopianmed@gmail.com
www.ethiopianmedicalass.org
Copyright © Ethiopian Medical Association 2020 All rights Reserved.