ማህበሩ ሁሉንም ሶሳዪቲ ወክሎ የሚቆም ጠንካራ ማህበር ማድረግ አለብን

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ከዘጠኙም ቅርንጫፍ ማህበራቱና ሶሳይቲዎች ጋር ሲመካከር የዋለ ሲሆን
ዶ/ር አበበ በቀለ የሌሎች አገራት ተሞክሮን ዋቢ በማድረግ ባቀረቡት ጥናታዊ ጽሁፍ ማህበሩ የህክምና ሙያውንም ሆነ ሃኪሙን ከመወከልና ከማገልገል አንጻር ሚናው የጎላ እንዲሆን ማህበሩ እንደ ማህበር መቀጠል፣ ወደ ቦርድነትና ኮሌጅነት ማደግ ይኖርበታል፡፡
በውይይቱ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የሶሳዪቲዎች ጋር ያለው ግንኙነት ከማህበራት ወንድማማችነት መውጣት አለበት፣የሶሳዪቲ መብዛት የሳይንሱን ማደግ ምልክት እንጂ የኢ.ህ.ማን የሚያዳክም መሆን የለበትም የሚሉ ተደጋጋሚ ሃሳቦች የተንጸባረቁበት ነበር፡፡

በውይይቱ ሶሳይቲያቸውን ወክለው የመጡት ተሳታፊዎች ሲናገሩ ለብቻችን ሄደን ልናሳካ ያልቻልናቸውን ጥያቄዎቻችንን መልስ ልናነኝ የምንችለው አብሮ በመስራትና ማህበሩ ሁሉንም ሶሳዪቲ ወክሎ የሚቆም ጠንካራ ማህበር ስናደርገው ነው ብለዋል፡፡

በመሆኑም ሊያሰራ የሚችል የረጅም የመካከለኛና የአጭር የጋራ ስትራቴጂክ እቅድ አውጥቶ በቶሎ ወደ ትግበራ መግባት አለበት የሚል ስምምነት ተደርሷል፡፡
ፕሮፌሰር ማርቆስ ተስፋዬ ስለ አባልነት ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ሃኪም እንደ ሃኪምነቱ የኢ.ህ.ማ አባል መሆን ይገባዋል በሶሳዪቲና በማህበሩ መሃል ልዩነት መፈጠር የለበትም የሚል ሃሳብ ተነስቶበታል፡፡

ስለ ማህበሩ ህንጻ ግንባታም መሬቱ የተሰጠው ለሃኪም እስከሆነ ድረስ ሁሉም ሃኪም ሁሉም ሶሳዪቲ በባለቤትነት ስሜት ለህንጻው ግንባታ የራሱን ድርሻ መወጣት አለበትም ተብሏል፡፡
በዶ/ር ትህትና ንጉሴ የማህበሩን 54ኛ ጉባኤ በማስመልከት ገለጻ የተሰጠ ሲሆን ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዘንድሮው የማህበሩ 54ኛ ጉባኤ ከጥር 14-20/2010 ድረስ በአዳማ፣አሰላ፣ጥቁር አንበሳ፣ጳውሎስ፣ዘውዲቱ፣አያት እና ቤተል ሆስፒታሎችና የህክምና ኮሌጆች የደም ልገሳ የሚደረገ ሲሆን የህክምና ባለሞያው የደም ልገሳው የተዋጣ እንዲን መቀስቀስ እንደሚኖርባቸው ዶ/ር ትህትና አሳስበዋል፡፡
ፓናል ውይይቶች ርዕስም

ጥራት ለህክምና ትምህርት፣ጥራት ለህክምና አሰጣጥ እና ጥራት ለህክምና አቅርቦት ላይ ሲሆን state of the ART lecture ሶሳይቲዎች አቅራቢና ርዕስ መምረጥ ድርሻን እንዲወስዱም ተብሏል፡፡
እንዳለፉት አመታት ሁሉ ለሶስተኛ ግዜ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ሩጫም ይኖራል፡፡