ሂኪም ወርቅነህ እሸቱ 154 የልደት በአል

ለህክምና ባለሞያዎች የሚሰጥ ዕውቅና በጤናው ዘርፍ ለሚፈጠሩ ሁሉን አቅፍ ለውጦች ትልቅ አስተዋፅኦ አለው በሚል መርህ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የሂኪም ወርቅነህ እሸቱ 154 የልደት በአል ምክንያት በማድረግ ዝክረ ሀኪም ወርቅነህን ከባለድርሻ አካላት ጋር አክብሯል፡፡

ሂኪም ወርቅነህ እሸቱ

የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር ከራስ ሚዲያ እና ፐሮሞሽን ጋር በመተባበር ጥቅምት 11 ቀን 2011ዓ.ም ዝክረ ሀኪም ወርቅነህን የሚዲካል ዳይሬክተር ሆነው ባገልገሉበት እና በኢትዮጵያ የመጀመሪያ በሆነው ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል የሀኪም ወርቅነህ ቤተሰቦች ፣ የኢትዮጵያ ህክምና ማህበር የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ አርቲስቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የተከበረ ሲሆን ማህበሩን በመወከል ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አበባው ፈቃዱ በ3 ዓመታቸው ከቤተሰቦቻቸው ተነጥለው የተወሰዱት ሀኪም ወርቅነህ ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ሀገራቸው በመመለስ በጤናው ዘርፍ ያደረጉት አስተዋፅኦ በህክምናው ዘርፍ ለተሰማሩት የህክምና ባለሞያዎች ሁሉ በአርአያነት ሊዘከር የሚገባው መሆኑን ገልፀዋል፡፡