
በአገራችን የሙያ ማህበራት መቋቋም ረጅም ታሪክ ያለው ቢሆንም ለሙያ ማህበራት መደራጀት እና ማደግ ምቹ የሆነ የሕግ ማዕቀፍ ባለመኖሩ ምክንያት ዘርፉ በማህበራዊ፣ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ውስጥ የሚገባውን ሚና እንዳይጫወት ማድረጉን የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ጂማ ዲልቦ ተናግረዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የሙያ ማህበራት በተሻለ ሁኔታ ለመምራትና ለመደገፍ እንዲቻል በቅርቡ ተጠንቶ በጸደቀው አዲስ የባለሥልጣን መ/ቤታችን መዋቅራዊ አደረጃጀት አንድ ራሱን የቻለ “የሙያ ማህበራት ዴስክ” ያለው መሆኑን በማንሳት ይህ ዴስክ በቀጣይ ለሙያ ማህበራት የሚደረጉ ድጋፎችን በተደራጀና በተጠና መንገድ ለማከናወን እንደሚያግዝ ይታመናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡



ከሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የፌስቡክ ገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚገልጸው በፕሮግራሙ ላይ የጉባኤው መተዳደሪያ ደንብን ጨምሮ በርካታ መነሻ ጹሑፎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን በመጨረሻም የጠቅላላ ጉባኤዉን ሰብሳቢ ም/ሰብሳቢ ፡ፀሃፊ እንዲሁም ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚ አባላትን በመምረጥ ተጠናቋል፡፡
የኢትዮጵያ ህክምና ማህበርም ለዚህ ጥምረት መቋቋም ጉልህ አስተወፅኦ ካደረጉ ተቋማት አንዱ ሲሆን ከተመረጡት ዘጠኝ የስራ አስፈጻሚ አባላት መካከል የኢትዮጵያ ሕክምና ማህበር ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር የሆኑት ትዕግስት መኮንን ይገኙበታል፡፡